
Grade Five
Computer Training for grade five students
መግቢያ
የሰው ልጅ የሚያከናውናቸው ስራዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸውና በየጊዜው የሚገጥሙትን ችግሮች ለመፍታት እንዲረዳው እንዲሁም የተቀላጠፈ እንዲሆን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲፈጠሩ ተደርጓል። እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጀመሪያ አካባቢ እንደ ስልክ፣ ራዲዮ፣ የ ሂሳብ ስራዎችን ለመስራት የሚያገለግሉ እንደ ካልኩሌተር ያሉ ነበሩ። እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እየተሻሻሉ መጥተው ዛሬ የምንጠቀምባቸው የመረጃና የመገናኛ መሳሪያዎች ተፈጥረዋል።
ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT)
ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተለያዩ የኮምፒውተር ስርዓት ስብስቦች ማለት ነው። ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ሚና አለው። ይህም የተለያዩ ተግባራትን፣ የስራ ሂደቶችን ያቀላጥፋል፣ ጥራት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ ወጪን ይቀንሳል፣ ስራዎችን ያቀላል፣ እንዲሁም ሰዎች እርስ በእርሳቸው ግንኙነት እንዲፈጥሩ ያስችላል።
ኮምፕዩተር፡- ማንኛውንም መረጃ የሚይዝ፣ የሚተነትን እንዲሁም ለመገናኛነት የሚያገለግል መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክ ዕቃ ወይም ማሽን ያመለክታል፡፡ ምሳሌ ፡- ዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ ታብሌት፣ ካልኩሌተር፣ ስማርት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ---- |
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እድገት መረጃን መለዋወጥን እጅግ አስፈላጊ ስላደረገው፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ Information and Communication Technology (ICT) እንዲፈጠር ምክንያት ሆ ኗል። ይህም መረጃን መለዋወጥ እጅግ ፈጣንና ቀላሉ እንዲሆን አድርጎታል። ለምሳሌ፦ ኢንተርኔት
ሙሉውን የስልጠና መጽሐፍ ለማኘት የስልጠና ቪዲዮ ለመመልከት ለመመዝገብ
Power in Numbers
3
Programs
25
Locations
Volunteers
