‘ሚስቶቻቸውን በቤት ውስጥ ሥራ ለማገዝ ሥልጠና የሚወስዱት ወንዶች
- Adiheni multimedia provisions
- Jan 29, 2024
- 1 min read
Updated: Feb 8, 2024
ከዕለቱ ዜናዎችና መረጃዎች የተቀነጨበ 👉 ያድምጡ AH online radio & Podcast
ሴቶች በቤት ውስጥ ያለባቸውን የሥራ ጫና ለመቀነስ በኡጋንዳ ያለ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወንዶች ሚስቶቻቸውን በቤት ውስጥ ሥራ እንዲያግዙ ሥልጠና እየሰጠ ነው። ሥልጠናው በተለይ ልጆችን በማጠብ፣ ምግብ በማብሰል ውሃ በመቅዳት እና የቤት እና የአካባቢ ንጽህናን እንዲጠብቁ ወንዶችን የሚያበረታታ ነው። ይህ ሲሆንም ሚስቶች ሌሎች ሥራዎችን ለመሥራት እና ለመማር ዕድል ይፈጠርላቸዋል የሚል ሃሳብ አለ።
ባለፈው አመት በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው “የባሎች ትምህርት ቤት”እንደተከፈተ መዘገባችን ይታወሰል::
በሲዳማ ክልል በህፃናት አድን ድርጅት ድጋፍ ባሎችን በልጆች አያያዝ፣ ምግብ ማብሰል ፣ንጽህና አጠባበቅ እና ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ያተኮረ ትምህርት ቤት ተከፍቷል::
Comments