top of page
Search

ንብ አፍቃሪው የመናዊ

Updated: Oct 4, 2023

ከዕለቱ ዜናዎችና መረጃዎች የተቀነጨበ 👉 ያድምጡ AH online radio & Podcast




የመናዊው አብዱልጀባር አል ጎሊ በጦርነት በደቀቀችው ሀገሩ ከንቦች ጋር ይውላል። የስምንት አመቱ ጦርነት ገበያውን ቢያቀዘቅዘውም ለንቦችና ለማር ያለው ፍቅር እየጨመረ መሄዱን ይናገራል። “ለንቦች ፍቅሬን ለመግለጽ ፊቴ እና ሰውነቴን እንዲወሩኝ አደርጋለሁ” የሚለው አብዱልጀባር፥ ንቦችን በብልሃት መያዝ እንደሚገባ ያነሳል። እርሱ ግን ባህሪያቸውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እንደማይነድፉትና አንዳንዴ ቢገጥመው እንኳን “እንደ መሳም” እንደሚቆጥረው ለሬውተርስ ተናግሯል።


እንደ መንግስታቱ ድርጅት መረጃ በየመን ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በማር ምርት የሚተዳደሩ ሲሆን፥ ባለፈው አመት ብቻ ከ1 ሺህ 500 ቶን በላይ ማር ተመርቷል።




 
 
 

Comments


Post: Blog2 Post
bottom of page