ኩላሊቶቻችሁን ተንከባከቡ!
- Adiheni multimedia provisions
- Jan 29, 2024
- 2 min read
Updated: Feb 8, 2024
የጤና መረጃ ፣ በየሳምንቱ ይቀርባል 👉 ያድምጡ AH online radio & Podcast
በኢትዮጲያ የኩላሊት ህመምተኞች ብዛት እየጨመረው ያለው ለምንድን ነው? የኩላሊት ህመም ፣ መከላከያ መንገዶች እና ቅድመ ህክምናዎች ምንድናቸው? በነፃ የሚገኘው“ኩላሊትዎን ይታደጉ” የተሰኘውን መጽሐፍ የት ይገኛል?
መሬትና የሰው አካል የጋራ የሆነ ባሕርይ አላቸው:- ሕይወትን ጠብቆ ለማቆየት ሁለቱም ማጣሪያ ያስፈልጋቸዋል። መሬት ያለማቋረጥ ከፀሐይ የሚመጡትን ጎጂ ጨረሮች የሚከላከል ነገር ያስፈልጋታል። በከባቢ አየራችን ውስጥ የሚገኘው የኦዞን ንብር እነዚህን ጨረሮች አጣርቶ በማስቀረት ለሕይወት አስፈላጊ የሆነው ብርሃን ወደ መሬት እንዲያልፍ ያደርጋል። ሰውነትህስ? በሰውነትህ ውስጥ የሚካሄዱት አብዛኞቹ ኬሚካላዊ ሂደቶች መርዛማ የሆኑ ንጥረ ነገሮችና መወገድ ያለባቸው ሌሎች ነገሮች ወደ ደምህ እንዲገቡ ያደርጋሉ። እነዚህ ነገሮች ካልተወገዱ ከባድ ችግር አልፎ ተርፎም ሞት ሊያስከትሉብህ ይችላሉ። ዘወትር መጣራትና መወገድ አለባቸው። ይህ የማጣራት ሥራ ኩላሊቶችህ ከሚያከናውኗቸው ዋና ዋና ተግባሮች አንዱ ነው።
ኩላሊት አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን እና መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን በማስወገድ ሰውነታችን ንፁህ እና ጤናማ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ የሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዋነኛዉ ነዉ። ምንም እንኳን ዋናኛ የኩላሊት ተግባር መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ማስወገድ ቢሆንም ብቸኛ ተግባሩ ግን አይደለም። የደም ግፊትን በማስተካከል በሰውነት ውስጥ ያለውን ፈሳሽ እና ንጥረነገሮችን መጠን በመቆጣጠር ረገድም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አብዛኞቻችን ሁለት ኩላሊቶች ይዘን ብንወለድም ሁሉንም አስፈላጊ ሥራዎችን በብቃት ለመወጣት አንድ ኩላሊት ብቻ በቂ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአሳሳቢ ሁኔታ በስኳር እና በከፍተኛ የደም ግፊት ህመም የሚሰቃዩ ሕመምተኞች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የኩላሊት ህመም የሚሰቃዩ ታካሚዎች ቁጥር በተመሳሳይ እንዲጨምር ገፊ ምክንያት ሆኗል። ይህ ደግሞ ስለ ኩላሊት ህመም ፣ መከላከያ መንገዶች እና ቅድመ ህክምና የተሻለ ግንዛቤና መረዳትን ማዳበር ላይ ቀሪ የቤት ሰራዎች እንዳሉብን አመላካች ነዉ።
በኩላሊትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ቢቢሲ ዶ/ር ፍጹም ጥላሁንን አናግሯቸው ነበር። ዶ/ር ፍጹም ነዋሪነታቸው በአሜሪካን አገር ሲሆን የኩላሊት ሕክምና ከፍተኛ ስፔሻሊስት ናቸው። የኩላሊት ህመምተኞች ብዛት የጨመረው ለምን እንደሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር በተለይ በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኩላሊት ህመምተኞች ይታያሉ። በቤተሰብ፣ በጓደኛ ደረጃ በቅርብ የምናውቃቸውም የኩላሊት ታማሚዎች በዝተዋል። እንዲህ የኩላሊት ህመም የተስፋፋው ምን አዲስ ነገር ተከስቶ እንደሆነ ተጠይቀው ነበር፡፡ እሳቸውም መልስ ሰተውበታል፡፡
ሰፊ ጥናት የሚፈልግ ጉዳይ ቢሆንም ሁለት ምክንያቶች እንዳሉ ነው የምገምተው ይላሉ ዶ/ር ፍጹም። አንዱ የአኗኗር ዘይቤያችን መቀየሩ ሊሆን ይችላል። "አብዛኛው ሰው ወደ ከተማ ገብቶ መኖር ጀምሯል። ቢሮ ነው የሚሠራው፤ ቢሮ ስንቀመጥ እንቅስቃሴ ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ያደርጋል። "የሰውነት ክብደት ሲጨምር የስኳርና የደም ግፊት በሽተኞችም እየጨመሩ ይመጣሉ። እነዚህ ደግሞ በዋናነት የኩላሊት በሽታን የሚያመጡ ነገሮች ናቸው። የከተሜ የአኗኗር ዘይቤ መበርከት አንዱ ምክንያት ከሆነ ሌሎች ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ምናልባት የኩላሊት ህመም ታማሚ በዝቶ የታየን ምርመራ በመስፋፋቱ ምክንያትም ሊሆን ይችላል ብለው ይጠረጥራሉ ዶ/ር ፍጹም። "በፊት ሰው 'ታመመና ሞተ' ይባላል እንጂ በምን ሞተ? የሚለው ጥያቄ አልነበረም። ወይም መልስ አልነበረመው። አሁን ግን ምርመራ ስላለ ሰዎች በኩላሊት ህመም መሞታቸውን በስፋት ማወቅ ጀምረን ሊሆን ይችላል።"
ዶ/ር ፍጹም አንድ ሌላ መላምት አድርገው የሚያስቀምጡት የምርመራ አቅም መጨመር ነው። ለምሳሌ በፊት የኩላሊት ዕጥበት (ዳያሊሲስ) አይታወቅም ነበር። የታመመ ሰው ይሞታል። አሁን በኩላሊት ዕጥበት ላይ ያሉ ብዙ ሰዎችን እናውቃለን። ይህም ኩላሊት ህመም የበዛ እንደሆነ እንዲሰማን አድርጎም ይሆናል። መድኃኒት በብዛት እየቃምን መሆኑ ኩላሊት ታማሚን አብዝቶብን ይሆን? ዶ/ር ፍጹም ይህ ነገር በብርቱ ያሳስባቸዋል። "በተለይ ትልቁ ችግር በእኛ አገር ሐኪም ሳይሆን በሽተኛው ራሱ ነው ለራሱ መድኃኒት የሚያዘው" ይላሉ። ይህ እንዴት ችግር እንደሆነ ሲያብራሩ ብዙ ሰው የኩላሊት ህመም እንዳለበት አለማወቁን ያነሳሉ። ሰዎች ሌላ ህመም ሲታመሙ ነው ኩላሊት የሚመረመሩት። እስከዚያ ድረስ ግን ጤነኛ ኩላሊት እንዳላቸው ነው የሚገምቱት። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ታዲያ እንደልባቸው መድኃኒት ይወስዳሉ። ለሌላ በሽታ መድኃኒት ሲወስዱ የኩላሊታቸው ጤና ስለማይታወቅ የመድኃኒት ምጣኔ ሳይሠራላቸው መድኃኒት ይወስዳሉ። ያለ ኩላሊት ምርመራ መድኃኒት በፈቃዳችን ስንወስድ ደግሞ ኩላሊት ላይ ጫና ይፈጠራል። "ስለዚህ በእኛ አገር ሁኔታ መጀመሪያ ማስቆም ያለብን ሐኪም ሳያዝ መድኃኒት መውሰድን ነው" ይላሉ።
ሁለተኛ በብዛት ገበያ ላይ ካሉ መድኃኒቶች ውስጥ ሰው በራሱ ተነሳስቶ የሚወስዳቸው የራስ ምታት፣ የቀርጥማት ማስታገሻ መድኃኒቶች ችግር እየሆኑ መጥተዋል። እነዚህን መድኃኒቶች ሰው ዝም ብሎ ነው የሚገዛቸው። መድኃኒቶቹ ተደጋግመው በሚወሰዱበት ጊዜ ኩላሊታችን ላይ ጫና ይፈጥሩበታል። የጨጓራ መድኃኒቶችም ተመሳሳይ ችግር ኩላሊት ላይ ይፈጥራሉ። ያለ ሐኪም ትዕዘዝ የምንወስዳቸው ከሆነ በተለይ ኩላሊታችን ሊጎዱ ይችላሉ። መድኃኒትን ሐኪም ሲያዝልን ብቻ ብንወስድ ጥሩ ነው። ለምን ከተባለ አንደኛ ሐኪማችን ትክክለኛውን መጠን ይነግረናል። ሁለተኛ ደግሞ የኩላሊታችንን ሁኔታ መርምሮ መውሰድ የሌለብንን መድኃኒት ያሳውቀናል። ዶ/ር ፍጹም እንደሚሉት በተለይ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች በቀላሉ ተገኙ ተብሎ በየጊዜው እያነሱ መቃም አደጋ አለው።
ታዲያ ኩላሊታችንን እንዴት እንንከባከበው? ቁልፍ ተግባራትን የሚያከናውነው ባተሌው ኩላሊት አንድ ጊዜ ከታመመ ብዙ ጣጣ ይዞ ይመጣል። ብዙ ነገሮች ይስተጓጎላሉ። ብዙ ነገሮች ይወሳሰቡብናል። ምን ተሻለ ታዲያ ሲባሉ ዶ/ር ፍጹም አጭር ምክር ሰጥተው ያልፋሉ። ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል፣ እና ደግሞ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ። "ኩላሊታችንን አልታመምንም ማለት ኩላሊታችን ጤነኛ ነው ማለት አይደለም።"
የኩላሊት ህመም እንዴት እንከላከለዋለን? የሚገኘው“ኩላሊትዎን ይታደጉ” የተሰኘውን መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡፡
ኩላሊቶቻችን ፈፅሞ ችላ ማለት የለብንም። አስፈላጊ እና ዋና ዋና ኩላሊትን ከህመሙ መጠበቂያ እና መከላከያ መንገዶችን ሁለት መንገድ መመልከት ሲቻል እነሱም ጥንቃቄ ለጤናማ ሰው እና ጥንቃቄ ለኩላሊት ታማሚዎች ናቸው፡፡ ለጤናማ ሰው የሚረዱ የጥነቃቄ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
1. ንቁ እና ቀልጣፋ መሆን፡ -
መደበኛ ኤሮቢክ ስፖርት እና የዘወትር የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡ እንዲህ አይነት የአካል እንቅስቃሴዎች የስኳር እና የከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ተጋላጭነትን በመቀነስ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትንም ይቀንሳል።
2. የተመጣጠነ ምግብ፡- አትክልት እና ፍራፍሬ መመገብ። ፋብሪካ ውስጥ የተዘጋጁ ፣ ከፍተኛ ካሎሪ ያለባቸው ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ስኳር’፣ ስጋና ቅባት ያላቸው ምግቦችን መቀነስ። ከ40ዓመት በላይ ዕድሜ በሆኑት ዘንድ፤ የጨው መጠንን መቀነስ የኩላሊት ጠጠር እና የከፍተኛ የደም ግፊት ህመሙን ለመከላከል ይረዳል።
3. የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር
4. ሲጋራ ማጨስ እና የትንባሆ ውጤቶችን ማቆም
5. ከማዘዣ ዉጪ የሚሸጡ መድሃኒቶች መጠበቅ፡ -
የተለመዱ መድሃኒቶች እንደ አይቡፕሮፌን እና ናፕሮዜን በተደጋጋሚ ከመጠን በላይ ከተወሰዱ ኩላሊት ላይ ጉዳት በማድረስ መድከምን እንደሚያምጡ ይታወቃል።
6. በዛ ያለ ዉሀ መጠጣት፡ -
በቂ የሆነ ዉሀ መጠጣት (በቀን እስከ 3 ሊትር) ሽንትን ለማቅጠን፣ ከአካላችን የሚወጡ ቆሻሻ ነገሮችን ለማስወገድ እና የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ይረዳል።
7. ዓመታዊ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ፡- የኩላሊት ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ ዝምተኛ ስለሆነ፤ ከፍተኛ የሆነ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት ምልክት አያሳይም። ኩላሊታችሁን የምትወዱ ከሆነ በተለይ 40 አመት እድሜ ከሞላዎት በኋላ መደበኛ የሆነ የኩላሊት ምርመራ ማድረግዎን አይርሱ።
ሌላኛው ለኩላሊት ህመም ታካሚዎች የሚረዱ የጥንቃቄ መንገዶችስ የትኞቹ ናቸው? ወደ 12 የሚጠጉ ነጥቦችን በመጽሐፉ ላይ የቀረቡ ሲሆን መጽሐፉን እንዲያነቡ ተጋብዘዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ታካሚዎች ከኩላሊት ህመም ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች በመመለስ እና ስለህመማቸውየተሻለ ግንዛቤ በማስጨበጥ በተሻለ መልኩ ህመሙን ማከም እንዲያስችላቸው ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
መጽሐፉን በኤሌትሮኒክ ፎርማት አሊያም በፒዲኤፍ አውርዶ ለማንበብ ከስር ያለውን ገጽ ይመልከቱ፡፡

የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው?
የኩላሊት ጠጠር በኩላሊት ውስጥ የሚገኝ ከአሸዋ ቅንጣት እስከ የጎልፍ ኳስ ያህል መጠን ሊኖረው የሚችል እና መደበኛ ያልሆነ ቅርጽ ያለው ጠንካራ ክምችት (ክሪስታል) መሆኑ ይነገራል፡፡እንደሕክምናባለሙያዎችገለጻም÷ጠጠሮቹ ከሚኒራል፣ ዓሲድ እና ጨው የተሠሩ ጠንካራ የጠጠር ክምችቶች ናቸውየኩላሊት ጠጠር በሽንት ቱቦ ውስጥ ከገባ የሽንትን የፍሰት ሂደት በመዝጋት ኩላሊቱን እንዲያብጥ በማድረግ የሽንት ቱቦው እንዲተነፍስ ሊያደርግ እንደሚችልምያብራራሉ፡፡ ይህም ከባድ ህመም እንደሚያስከትል ነው የሚገልጹት፡፡
የኩላሊትጠጠርመንስዔምንድንነው?
ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት፣ አጋላጭ የጤና እክል እና አንዳንድ መድኃኒቶች ከብዙ የኩላሊት ጠጠር መንስዔዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን እንዲሁም ጨው እና ስኳር የበዛባቸው ምግቦችን አብዝቶ መጠቀም፣ በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር በምክንያትነት ይነሳሉ፡፡
የኩላሊትጠጠርንእንዴትመከላከልይቻላል? የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ለመከላከል የአመጋገብ ለውጥን ጨምሮ መደረግ ያለባቸው በርካታ ጥንቃቄች እንዳሉ ይታመናል፡፡ ለአብነትም÷ 3 ሊትር ውሃ በመጠጣት የሚወገደውን የሽንት መጠን 2 ነጥብ 5 ሊትር እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ ይመከራል፡፡
በተጨማሪም የአመጋገብ ባሕልን ማስተካከል (ለምሣሌ፡- የጨው መጠንና የፕሮቲን መጠናቸው የበዛባቸው ምግቦችን አለመመገብ፣ አትክልትና ፍራፍሬን መመገብ፣ የሥጋ ፍጆታን መቀነስ፣ በቂ ካልሺየም ያላቸውን ምግቦች መመገብ) የሚሉት የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ከሚረዱት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የኩላሊትጠጠርተጋላጮችእነማንናቸው? ተጋላጭነትን በተመለከተ ከጾታ አንጻር በአብዛኛው በወንዶች ላይ እንደሚከሰት ነው ባለሙያች የሚያስረዱት፡፡ በአጠቃላይ በጎልማሳነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን እንደሚያጠቃም ይገለጻል፡፡
የኩላሊትጠጠርህመምምልክቱምንድንነው? በአብዛኛው የኩላሊት ጠጠር ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል የህመም ዓይነት እንደሆነ ይገለጻል፡፡ ጠጠሩ ከተከሰተ በኋላ ግን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ ቱቦ በኩል በሚኖር ሂደት ህመም ስለሚፈጥር ምልክቶች መታየት እንደሚጀምሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
በአጠቃላይ የዘርፉ ባለሙያች የጋራ ካደረጓቸው ምልክቶች መካከል÷ ከፍተኛ የጎን ህመም ስሜት መኖር፣ ከጎድን አጥንት በታች የጀርባ ሕመም፣ ወደ ንፍፊትና ወደ ታችኛው የሆድ ክፍል ከፍተኛ ህመም መሰማት፣ ሽንት በሚወገድበት ወቅት የህመም ስሜት መኖር፣ የሽንት ቀለም መለወጥ (ቀይ፣ ቡኒ ወይንም ሮዝ መሆን) የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም የደፈረሰ እና መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት መኖር፣ አጣዳፊ የሽንት መኖርና ከሌላው ጊዜ በተለየ መብዛት የሚሉት የህመሙ ምልክቶች እንደሆኑ ይገለጻል፡፡ በኩላሊት ጠጠር ምክንያት የሚከሰት ህመም የጠጠሩን እንቅስቃሴ ተከትሎ ቦታውን ሊቀያይር እንደሚችልም ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡
ከላይ የተገለጹት የተለመዱ የኩላሊት ጠጠር ምልክቶች ሲሆኑ፥ በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የህመም ስሜት ካለ፣ ከፍተኛ የየውጋት ስሜት ሲኖር፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ከተከሰተ፣ ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት ሲፈጠር፣ ደም የቀላቀለ ሽንት ሲስተወልና ሽንት ለማስወገድ የመቸገር ሁኔታ ሲከሰት በአፋጣኝ ወደ ሕክምና መሄድ ይመከራል፡፡
የኩላሊት ጠጠር ሕክምና አለው? የኩላሊት ጠጠር ሕክምና እንዳለው ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ሕክምናው ግን እንደጠጠሩ ዓይነት እና መጠን እንደሚለያይም ነው ከሄልዝ ላይን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡
Comments