top of page
Search

በ2025 የታገዱ የምግብ ምርት ዓይነቶችና እርምጃ የተወሰደባቸው የምግብ አምራቾች


ree

የተለያዩ የገበታ ጨው ምርት ዓይነቶች በሚመለከተው አካል የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ ሳይሰጣቸውና ጥራትና ደረጃቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ በመገኘታቸው ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለስልጣኑ አሳሰበ፡፡


አዲስ አበባ፡ መጋቢት 4፣2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በቅርቡ ገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር አምስት የተለያዩ የገበታ ጨው ምርቶች የብሔራዊ የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ ሳያገኙ ምልክቱን ለጥፈው ገበያ ላይ ውለው ተገኝተዋል፤በመሆኑም እነዚህ ምርቶች ጥራታቸውና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለሰልጣኑ ያሳስባል፡፡


ምስላቸው እና ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተቀመጡ የተለያዩ የገበታ ጨው ምርቶች የብሔራዊ ደረጃ ምልክቱን የመጠቀም ፈቃድ ያላገኙና ጥራት እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆናቸው ያሳውቃል፡፡


1. ሊኑ የገበታ ጨው /LINU IODIZED SALT /፣


2. ታሪክ የገበታ ጨው /TARIK TABLE SALT /፣


3. SALT BAY፣


4. ሺማ አዮዳይዝድ ጨው /SHIMA IODIZED SALT/


5. እና ጂ.ኤም ኤዳይዝድ ጨው /G.M Iodized salt/ በሚባል የምርት ስም የሚጠሩ ናቸው።


ree

በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ላይ በተደረገ የገበያ የቅኝት ስራ የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡


አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በሰራው የገበያ ቅኝት ስራዎች 44 ዓይነት የምርት መለያ ስም ያላቸው የተለያዩ አዮዲን የበለፀጉ የምግብ ጨው በሚል ታሽገው ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ በተጨማሪም የሀገሪቱን አስገዳጅ ብሔዊ ደረጃ፣እና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ ሲቀርቡ የነበሩ ምርቶች መገኘታቸው አስታውቀዋል፡፡


በመሆኑም በየደረጃው ከሚካሄዱ በርካታ የቁጥጥሩ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የገበያ ቅኝት ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ምግቦች ላይ ባደረገው የገበያ ቅኝት በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው CES 70 2017 እና የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ያላሟሉ እና የደረጃ ምልክት ያለጠፉ ምርቶችን መለየት የተቻለ ሲሆን በምርቱ ላይ ስለምርቱ የተለጠፉ ወይም የተፃፉ የምርት ገላጭ ፅሁፍ የኢትዮጵያ እስታንዳርድ ኢንስቲቲዩት ያወጣው አስገዳጅ ደረጃ CES 73 2013 ያላሟሉ ሲሆን በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች የአምራች ድርጅት ስም ያልተጠቀሰ፣ የአምራች አድራሻ ያልተገለፀ፣አስገዳጅ የደረጃ ምልክት ወይም የበለጸገ ምግብ ሎጎ የለውም፣የምርቱ መለያ ቁጥር የሌለው፣የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያልተገለፀ፣የአዮዲን መጠን አልተጠቀሰ የመጠቀሚያ እና የማብቂያ ጊዜ የሌላቸው ምርቶች መሆናቸው ተለይተዋል፡፡


የተገኙ ምርቶች ዝርዝር

1. አበሩሰ አዮዳይዝድ ጨው

በምስል ለመመልከት

2. ዛክ የገበታ ጨው

3. ሉሉ የገበታ ጨው

4. ሙሪዳ አዮዳይዝድ ጨው

5. እቱ የገበታ ጨው

6. እቴቴ የገበታ ጨው

7. እፍታ ጨው

8. ኤልሳ የገበታ ጨው

9. ሴፍ የገበታ ጨው

10. NS አዮዳይዝድ ሳልት

11. ማሚ የገበታ ጨው

12. ሣሊህ የገበታጨው

13. እማ የገበታ ጨው

14. አዮዲን የገበታ ጨው

15. ቃና የገበታ ጨው

16. ሀርመኒ የገበታ ጨው

17. ውዛት አዮዳይዝድ ሳልት

18. ሐበሻ ባለ አዮዲን ጨው

19. ሪል የገበታ ጨው

20. ሸጋ የገበታ ጨው

21. ጆይ አዮዳይዝድ ሳልት

22. ኮከብ የገበታ ጨው

23. ስኬት የገበታ ጨው

24. ፎር ኤም አዮዳይዝድ ሳልት

25. አዲስ የገበታ ጨው

26. ኤመሬት ጨው

27. አስቤዛ የገበታ ጨው

28. ቶም የገበታ ጨው

29. በረከት የገበታ ጨው

30. ሜናታ የገበታ ጨዉ

31. ቤስት አዮዳይዝድ ጨዉ

32. አፊአ የገበታ ጨው

33. ዋን በአዮዲን የበለፀገ የገበታ ጨዉ

34. አቢሲኒያ የገበታ ጨዉ

35. ማሩ የገበታ ጨዉ

36. ባና ኤዳይዝድ ጨው

37. ማራኪ ጨዉ

38. መክሊት የገበታ ጨዉ

39. ዳግም የገበታ ጨዉ

40. አዲስ የገበታ ጨዉ

41. አፍያ ጨዉ

42. ኦማር የገበታ ጨው

43. ገዳ የገበታ ጨው

44. NITSUH IODIZED SALT



ህገወጥ ለምግብነት የማይውል ጨው በማምረት ወደ ህብረተሰቡ ሲያሰራጩ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡


አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ንማኔ እንደገለጹት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከብሔራዊ ደህንነት፣ ከሲዳማ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከሀዋሳና ከለኩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመሆን በጋራ ባካሄዱት የሰርቬይላንስ ስራ ሸጋ፣ ሺማና ልዩ አዮዳይዝድ ጨው በሚል ህገወጥ የንግድ ስም ለምግብነት መዋል የሌለበተን ጥሬ ጨው አዮዳይዝድ ጨው በማለት በሀዋሳና በለኩ ከተሞች በድብቅ ሲያመርቱ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን የህገወጥ ተግባር በሚከናወንበት ስፍራ በተደረገ ፍተሻ የማምረቻ ቁሳቁሶች ፣ ተመርተው ለማሰራጨት የተዘጋጁ ለምግነት የማይውል ጨውና በተለያየ የንግድ ስም የተዘጋጁ ማሸጊያዎች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡


በተጨማሪም የሲዳማ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦሪሶ ቡላሾ አጥፊዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን የምርቶቹ ናሙና ወደ ለብራቶሪ መላኩ ገልጿል፡፡


የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ባካሄደው የድህረ ገበያ ጥናት በህገወጥ መንገድ ተመርተው ወደ ገበያ ሲሰራጩ የነበሩ 44 ዓይነት ህገወጥ የገበታ ጨው ምርቶች ህብረተሰባችን እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡


ከላይ የተጠቀሱት ህገወጥ ጨው አምራቾች ከነማምረቻ ንብረቶቻቸው ለመያዝ በተደረገው ኦፕሬሽን ህብረተሰባችን ላደረገው ትብብር እያመሰገንን መሰል ድርጊቶችን ለመጠቆም በነፃ የስልክ መስመር 8482 አልያም በአቅራቢያዎት ለሚገኝ ተቆጣጣሪ አካል ጥቆማ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡


የስቴሽነሪ ዕቃዎች / Stationeries
Buy Now

 
 
 

Comments


Post: Blog2 Post
bottom of page