top of page
Search

በ2023 እና 2024 የታገዱ የምግብ ምርት ዓይነቶችና እርምጃ የተወሰደባቸው የምግብ አምራቾች

Writer: Adiheni multimedia provisions Adiheni multimedia provisions

Updated: Feb 8, 2024

ከዕለቱ ዜናዎችና መረጃዎች የተቀነጨበ 👉 ያድምጡ     AH online radio & Podcast



የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን  ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶችን አሳወቀ


በያዝነውጥር/2016ዓ.ምየኢትዮጵያምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨውና የምግብ ዘይት ላይ አደረኩት ባለው የገበያ የቅኝት ስራ የገላጭ ጽሁፍ እና የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶች መኖራቸውን ገልጿል። ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል። የምግብ ዘይት እና በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ እንዲያሟሉ ደረጃ የወጣላቸው ሲሆን በነዚህ ምርቶች ላይ የደረጃ ምልክት አለመለጠፍ ከፍተኛ የህግ ጥሰት መሆኑ ተገልጿል።

አንድ ምርት ፦

* አገዳጅ የደረጃ ምልክት 

* የምርት መለያ ቁጥር

* የአምራች ስም 

* የአምራች አድራሻ

* የተሰራበት_ግብዓት

* የተመረተበትና የመጠቀሚያ ጊዜው  የሚያበቃበት ቀን ሊኖረው ይገባል።

በገበያ ላይ የዋሉ ምርቶችን የገበያ ቅኝት ስራዎችን በማጠናከር እና የቁጥጥር መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ እራሱ የቁጥጥር ባለቤት እንዲሆን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰራው የገበያ ቅኝት ስራዎች እንዳረጋገጠው   44 ዓይነት የምግብ ዘይት ምርት እና 39 ዓይነት አዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ምርት  ደህንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡ እንዲሁም የሀገሪቱን አስገዳጅ ደረጃ እና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ መገኘታቸው አስታውቀዋል፡፡


የምርት ገላጭ ፅሁፍ ማሟላት ለተጠቃሚው የመብት ጉዳይ በመሆኑ የምግብ ዘይት እና በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ እንዲያሟሉ ደረጃ ወጥቶላቸዋል፡፡ ምርቱን ለምግብነት የሚጠቀም ሰው ምርቱ ከምን እንደተመረተ የሚያውቅበት ፣ የመጠቀምያ ጊዜ የሚያበቃበትን የሚለይበት፣ በምርቱ ላይ የጥራት ችግር ቢከሰት በአምራች ወይም በተቆጣጣሪው ተጠቃሚው ምርቱን እንዳይጠቀም ከገበያ እንዲሰበሰብ ለማድረግ የሚጠቅም ምርት የሚለይበት መለያ ቁጥር ፣ የአምራች ስም እና አድራሻ አለመጠቀሱ እና  በኢትዮጵያ የሚወጡ አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶች ላይ የደረጃ ምልክት አለመለጠፍ ከፍተኛ የህግ ጥሰት ከመሆኑም በላይ አምራች ድርጅቱ ከምርት ጥራት ችግር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች ኃላፊነት ላለመውሰድ የሚያደርገው ጥረት በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህን ተገንዝቦ በገበያ ላይ የዋሉትን የምግብ ዘይት እና በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ምርቶች ከመግዛቱ በፊት የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ምልክት የለጠፉ ስለመሆኑ እና የምርት ገላጭ ፅሁፍ በአግባቡ ስለመጠቀሱ ከምርት ላይ ነቅሶ በመለየት በቂ መረጃ የሌላቸው ምርቶች እንዳይጠቀም አሳውቋል፡፡

 

በተጨማሪም ከላይ እንደተጠቀሰው በተሰራው ገበያ ቅኝት ለጥንቃቄ የምርቶቹን ዓይነትና የተገኙ ክፍተቶች በምስልና በስም ተዘርዝረው እንደሚከተለው ተጠቅሰዋል፡፡  


                         አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያማሉ ገበያ ላይ የተገኙ 

የምግብ ዘይት ምርቶች ዝርዝር 

የምግብ ጨው

1. ሰመር  ንፁህ የምግብ ዘይት 

1.    አርኪ የገበታ ጨው  ARKY IODIZED SALT

2. ማሚ የተጣራንፁህ የምግብ ዘይት

2.    ኢኮ  አዮዳይዝድ ጨው EKKO IODIZED SALT

3. እስካይ  /Sky Sun flower oil

3.    ስጦታ ጨው  SITOTA Iodized Salt

4. ሳኒ /SANI  Edible Cooking Oil)

4.    መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFIND & IODIZED SALT

5. አዚማር/Azimar Sunflower Oil

5.    አስቤዛ የገበታ ጨው  Asbeza Iodized salt

6. ኑራ ንፁህ የምግብ ዘይት

6.    ዘሀራ የገበታ ጨው  ZAHARA IODIZED SALT

7. አበባ ንፁህ የምግብ ዘይት

7.    መነስ ጨው MENES IODIZED SALT

8. አደይ ንፁህ የምግብ ዘይት

8.   ግዩን አዮዲን ጨው Ghion Iodin Salt

9. ዘቢብ/Zebib Sunflower oil

9.    አርዲ የገበታ ጨው  ARDI IODIZED SALT

10. አስሊ ንፁህ የምግብ ዘይት

10.    ሳሊህ የገበታ ጨው  SLIHA IODIZED SALT

11. ሪል (Real Pure Food Oil)

11.    ናና ጨው NANA SALT

12. ዙፋን ንፁህ የምግብ ዘይት

12.    ቤስት የገበታ ጨው Best Iodized Salt

13. ሀኒ(Hani Sunflower Oil)

13.    ቅመም የገበታ ጨው Iodized Salt

14. ዲና ንፁህ የምግብ ዘይት

14.    ረሃ የገበታ ጨው REHA IODIZED SALT

15. ሊና ንፁህ የምግብ ዘይት

15.    አርዲ የገበታ ጨው ARDY IODIZED SALT

16. ማማ የተጣራ የምግብ ዘይት

16.    አፊአ የገበታ ጨው AFIA IODIZED SALT

17.  አል ኑር Al-Nur Sunflowor Oil

17.    ፋና የገበታ ጨው  Fana table salt

18. ዋሪዳ Warida sunflower Oil

18.    እቴቴ የገበታ ጨው  Etete Iodized Table Salt

19. ዜድ ንፁህ የምግብ ዘይት

19.    ልዩ ጣዕም የገበታ ጨው  LIYU TAEM IODIZED Salt

20. ደሴት ንፁህ የምግብ ዘይት

20.    ሀሮኒ  HARONI Table Salt

21. ከፍታ ንፁህ የምግብ ዘይት Pure Food Oil

21.    ሮም  ROME  ንጹሁ የገበታ ጨው

22. ንግስት ንፁህ የምግብ ዘይት Nigist pure Food oil

22.    ቶፕ የገበታ ጨው  TOP IODIZED SALT

23. ሸገር Sheger pure Edible Oil

23.    ጤና ጨው Tena Iodized salt

24. አሪፍ Arif  የኑግ የምግብ ዘይት 

24.     ማሬ የገበታ ጨው  MARE IODIZED SALT

25. አመለ AMEL Edible Oil

25.     ሳፊ የገበታ ጨው  SAFI IODIZED SALT

26. ብሉ የኑግ ዘይት

26. እሜቴ  አዮዳይዝድ  የገበታ ጨው  Iodized Table Salt

27. ንፁህ Nitsuh Food Oil

27.     ሀላል የገበታ ጨው  HALAL IODIZED SALT

28. ኡማ ንፁህ የምግብ ዘይት 

28.     ጡልት ጨው TULIT SALT

29. ማዕድ Maed ንፁህ የምግብ ዘይት

29. ሪል የገበታ ጨው  REAL IODIZED SALT

30. ሀያት የተጣራ የምግብ ዘይት 

30.     ጎልድ GOLD IODIZED SALT

31. የምስራች ንፁህ የምግብ ዘይት

31.     ስፔሻል የገበታ ጨው  SPECIAL Iodized Table Salt

32. ህብረት ንፁህ የምግብ ዘይት

32.     ሰላም  የገበታ ጨው  IODIZED SALT

33. ጎንደር የምግብ ዘይት Gonder Food Oil

33.     ሸሙ በአዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው  SHEMU  IODIZED SALT

34. ዜማ Zema pure Edible Oil

34. ኢምሬት ጨው Emirate salt

35. ፋና fana

35.     ኑር NUR IODIZED SALT

36. ናና የኑግና የለውዝ የምግብ ዘይት 

36. ሀገሬ አዮዳይዝድ ጨው  HAGERE  Iodized Salt

37. ሪም ንፁህ የምግብ ዘይት

37.     ኢቲ ኤምኢየገበታ ጨው  ET ME IODIZED SALT

38. አንድነት ANDNET

38. ማራኪ MARAKI  በአዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው

39. ሲያም ንፁህ የምግብ ዘይት

39.     ታሪክ የገበታ ጨው TARIK TABLE SALT

40. ቤላ  የምግብ ዘይት

 

41. ሐሊማ  የምግብ ዘይት

 

42. ወሲላ ንፁህ የምግብ ዘይት Wesila

 

43. ዝና ንጹህ የምግብ ዘይት

 

44. ሰነዓ ንጹህ የምግብ ዘይት

 



በ2023 የታገዱ የምግብ ምርት ዓይነቶችና እርምጃ የተወሰደባቸው የምግብ አምራቾች

በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ2023 ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የታገዱ የምግብ ምርት ዓይነቶችና የተለያዩ ክፍተቶች መሰረት ተደርጎ እርምጃ የተወሰደባቸው የምግብ አምራቾች

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በያዝነው በጀት አመት በመጀመሪያው  አራት ወራት ውስጥ የምግብ ደህንነትና ጥራት ለማረጋገጥ በ104 የምግብ አምራቾች ላይ የድህረ ፍቃድ ቁጥጥር በማድረግ  የታዩ የተለያዩ ክፍተቶችን መሠረት በ13 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።


የባለስልጣኑ ምግብ ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙላት ተስፋዬ የ2016 በጀት አመት በአራት ወራት አፈጻጸም አስመልክተው እንዳስታወቁት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት በተለያዩ 104 የምግብ አምራቾች ላይ የድህረ ፍቃድ ቁጥጥር አድርጓል፡፡


በዚህም መሰረት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2 የታሸገ ዉሃ አምራች፣ በ4 የዱቄት ፋብሪካና ብስኩት አምራቾች፣ በ2 የፍላቨር ጁስ መጠጥ፣ በ2 የአዮዳይዝድ ጨዉ፣ በ1 የምግብ ዘይት አምራች፣በ1 ቴስቲ ሶያ አምራች እና በ1 የወተት አምራች በድምሩ በ13 የምግብ አምራቶች ላይ ቁጥጥር ማደረጉን ገልጸው በቁጥጥር ወቅት በታዩ የተለያዩ ክፍተቶች መሰረት ተደርጎ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

ለምርት ደህንነት አስጊ የሆነ ደካማ የመልካም አመራረት ችግር፣ የሶስተኛ ወገን የላብራቶሪ ውጤት ምርት መውደቅ፣ ቴክኒካል ባለሙያዎች ሳይኖሩ ምርት ሲያመርቱ መገኘት፣ የአዮዲን መጠንና አለማሟላት፣ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ጥሬ እቃ መጠቀም ፣የብቃት ማረጋገጫ አለማሳደስ እና የተሳሳተ ገላጭ ጽሁፍ መኖር ከታዩት ክፍተቶች መካከል ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው።


በአጠቃላይ በቁጥጥር ወቅት በተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት ክፍተታቸዉን አስተካክለዉ እስኪረጋገጥ ድረስ 13ቱ ፋብሪካዎች ምርት አምርተዉ ለህብረተሰቡ እንዳያቀርቡ እገዳ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተጣለ ሲሆን በተጨማሪም 2 አምራቾች ምርታቸዉን ከገበያ እንዲሰበስቡ መደረጉን አቶ ሙላት አብራረተዋል፡፡


ይህበንዲእንዳለባለፈውዓመትግንቦትወርላይ91የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው በባልስልጣኑ መታገዳቸውን ይፋ መደረጉ ይታወሰል፡፡


እንደባለስልጣኑ መረጃ በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ሳያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ ያሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል። የተከለከሉትም በአጠቃላይ 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች መሆናቸውን አስታውቋል። 46 ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው፣ 27 ዓይነት የምግብ ዘይት፣ 10 ዓይነት ከረሜላ ፣5 ዓይነት አቼቶ 2 ዓይነት የለውዝ ቅቤ እና አንድ የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን እንደሚገኙበት ተገልጿል።


ባለስልጣኑ በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣ የአምራች ድርጅታቸው ስም፣ አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣ መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ ያልተገለጸና የሌላቸው በመሆኑ የተነሳ ነዉ። ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።


ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ይፋ በማድረግ ህብረተሰቡ በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጠይቋል። በዚህም የተከለከሉ የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ስማቸው እንዲሁም ምስላቸው የሚከተሉት ናቸው ::





 
 
 

Comments


Post: Blog2 Post
bottom of page