top of page
Search

በኢትዮጵያ አዳዲስ የወባ ትንኝ ዝርያዎች አማካኝነት የሚተላለፉ አዳዲስ የወረሽኝ በሽታዎች እየጨመረ ነው ተባለ

Updated: Jan 26

ከዕለቱ ዜናዎችና መረጃዎች የተቀነጨበ 👉 ያድምጡ AH online radio & Podcast



ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2016

በኢትዮጵያ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዚህ በፊት በማይታወቁ የወባ በሽታ አምጭ ትንኞች የሚከሰት የወባ በሽታ ዓይነት እየጨመረ መምጣቱን፤ በፓን አፍሪካን የወባ ትንኝ መቆጣጠሪያ ማህበር የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ድልነሳው የኋላው ገልጸዋል። “የወባ በሽታ ባለፉት ዓመታት የወባ ስርጭት መጠኑ ቀንሶ የነበረ ቢሆንም፤ባለፉት ኹለት ዓመታት ዉስጥ ግን በወረርሽኝ ደረጃ በመላው አገሪቱ ተዳርሷል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።


ፕሬዝደንቱ አክለውም፤ የወባ በሽታ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ያልነበሩ እና ጠፍተው የነበሩ ትንኝ ወለድ በሽታዎች በስፋት እየተስተዋሉ መሆኑን ገልጸዋል። “ለአብነትም ደንጊ (Dengue fever) የተባለው በሽታ በስፋት በእስያ አካባቢ ይታወቅ የነበረ ቢሆንም በኢትዮጵያ የበሽታ ታሪክ በፈረንጆች 2013 ለመጀመሪያ ጊዜ ታይቷል፡፡” ካሉ በኋላ፤ በሽታው አድማሱን አስፍቶ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መታየቱን ጠቁመዋል። “በሽታው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ባህሪውን፣ መከላከያ መንገዱ እና የምርመራ ሂደቱ አለመታወቁ ትልቅ የኅብረተሰብ የጤና ችግር ሆኖ መጥቷል፡፡” ነው ያሉት። ለአብነትም በደቡብ ምዕራብ እስያ በስፋት የምትታወቀዋ አኔፌነስ ቴፈንሲ የተባለችው በሽታ አምጭትንኝ፤ ቀድምብሎ በጅቡቲ በመከሰት ከሰባት ዓመት በፊት ደግሞ የበሽታው ምልክት በኢትዮጵያ መታየቱን አመላክተዋል። ይህም ለመጀመሪያ የታየው በሶማሌ ክልል መሆኑን ጠቁመው፤ በመቀጠል በድሬድዋ፣ አፋር፣ መተሃራ፣ አዳማ፣ ወሎ፣ መተማ እንዲሁም በቅርቡ ጎጃም እና ቤኒሻንጉል አካባቢዎች የወባ ስርጭቱ መስፋፋቱን ገልጸዋል። ይኸው የወባ በሽታ በተመሳሳይም፤ ኬኒያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን መዛመቱን እና ወደ ምዕራብ አፍሪካ አገሮችም መስፋፋቱን ነው የጠቀሱት። እንዲሁም ቅልጥም ሰባሪ እና የቢጫ ወባ በሽታ የሚባሉት በሽታዎች ቀድሞም ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩ ቢሆንም፤ የስርጭት መጠናቸው በጣም አነስተኛ የነበረ ሲሆን፣ ከሦስት ዓመት ጀምሮ በአገሪቱ በርካታ ክፍሎች ላይ መታየት ጀምሯል ሲሉ ተደምጠዋል።

በኢትዮጵያ የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ግጭቶች በሽታውን ለመከላከል እና ስርጭቱን ለመቀነስ የሚሰሩ ሥራዎችን በማደናቀፍ የራሱ አስተዋጾ እንዳለው ገልጸዋል። እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ለወባ በሽታ መስፋፋት ጉልህ ድርሻ እንዳለው አመላክተዋል። የፓን አፍሪካ የወባ ትንኝ መቆጣጠሪያ ማህበር (PAMCA) ዘጠነኛው ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ሲሆን፤ ከመላው አለም ከ800 በላይ የሆኑ ሳይንቲስቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች የተሳተፉበት ነው። ይህ ጉባኤም አገር ዉስጥያ ሉትን ባለሙያዎች ከሌሎች አገራት ባለሙያዎች ጋር ትስስር የመፍጠርና ልምድ የመለዋወጥ እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ፤ በተለያዩ የአፍሪካ አገራትና በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ለጥናትና ምርምር ለፖሊሲ ግብዓት እንዲውል የማድረግና ምክረሃሳብ የማቅረብ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፓን አፍሪካ ወባት ንኞች መቆጣጠሪያ ማኅበር በኢትዮጵያ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን አቅዶ እየሠራ ሲሆን፤ ከጤና ሚኒስትር ጋር በመተባር በመሥራት ወደፊት የወባንና ትንኝ ወለድ በሽታዎች ለመቆጣጠርና ለማስወገድ በጋራ መሥራትና እቅዱን ይፋ የማድረግ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡ፕሬዝደንቱ አክለውም፤ “በአገር ደረጃችግር ላይነው ያለነው በበሽታው ከሚያዘውና ከሚሞተው እንዳለ ሆኖ በአገር የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡” ሲሉ አሳስበዋል

ከኢትዮጵያ አንድ ሚሊየን ስኩዌር ስፋት ዉስጥ 75 በመቶ የሚሆነው ቦታ ለወባ በሽታ የተጋለጡ መሆኑ እና ከዚህም ውስጥ 69 በመቶ የሚሆነው የኅብረተሰብ ክፍልም ተጋላጭ መሆኑ ማህበሩ አመላክቷል።



15 views0 comments

コメント


Post: Blog2 Post
bottom of page