top of page
Search

የግብረሰዶማዊነት፣ የፆታ መቀየር እና የውርጃ አጀንዳዎች በሰብአዊ መብት ሽፋን ስር

Updated: Feb 10

ከዕለቱ ዜናዎችና መረጃዎች የተቀነጨበ 👉 ያድምጡ     AH online radio & Podcast



የግብረሰዶማዊነት፣ የፆታ መቀየር እና የውርጃ አጀንዳዎች በሰብአዊ መብት ሽፋን ስር


ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባላት ጋር ለሚቀጥሉት 20 አመታት የሚቆይ ‘የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት’ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሳሞዋ በተባለች አገር “የሳሞአ ስምምነት” የተባለውን ሰነድ ባሳለፍነው ህዳር ወር 2016 ለመፈራረም ተገናኝተው ነበር።

ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት በወከሏት አምባሳደር አማካኝት የፈረመች ሲሆን ስምምነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተያዘው ጥር ወር እንደሚፀድቅ እና ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል ተብሏል።


ነገር ግን ‘ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግብረሰዶም እንታደግ’ ማህበር “በማር የተለወሰ እሬት የሆነ በትውልድ ላይ ሞት የሚያውጅ ስምምነት” ነው ብሏል። የኢኮኖሚ ትብብሩ እንዳለ ሆኖ ይህ ሰነድ በውስጡ ከያዛቸው የድጋፍ ስምምነቶች  ጀርባ ለድጋፉ ምላሽ ፈራሚ አገራቱ “አካታችነት” በሚል የተጠቀሱ ነጥቦችን እንዲያሟሉ ይገልፃል። ከእነሱም ውስጥ ግብረሰዶማዊነት፣ የፆታ መቀየር እና ውርጃን ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት የመሳሰሉ አጀንዳዎችን በሰብአዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የገቡበት በመሆኑ በበይነ መረብ የተቃውሞ ፊርማ ሲሰበሰብ አዲስ ማለዳ መመልከቷን ዘግባለች። 


ሀገራቱ “ይህ እንቅስቃሴአቸውን ከራሳቸው አልፎ በአለም ደረጃ ለማድረግ በየሀገራቱ መሰራጨት መጀመራቸውም የአደባባይ ሚስጥር ነው” የሚሉት በኢትዮጵያ የተቋቋመ የፀረ ግብረሰዶማዊነት ማህበር መስራች እና ሰብሳቢ መምህር ደረጀ ነጋሽ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት በግረሰዶም ላይ ያለው አቋም ከለዘብተኛም ባለፈ እንዲስፋፋ የሚፈልግ ነው። ለእርዳታ ብሎ መስማማቱ እና በየጊዜው እየጨመሩ መምጣታቸው የመከላከል ስራ እንደማይሰራ ማሳያ ነው በመሆኑም ምንም አይነት ቁርጠኝነት የለውም” ብለዋል። በተጨማሪም “በህዝቡ ፊት መቃወምን እያሳዩ  ከጀርባ ስምምነቶች መፈረም እና መሰል ድርጊቶችን ማድረግ አግባብነት የሌለው ነው” በማለት ገልፀዋል፡፡


ከዚህ ቀደም መሰል ድርጊቶች ጥቆማ እንዲሰርሱት የአዲስ አበባ ፖሊስ መግለጫ ይታውሳል፡፡  በጥቅምት እና ህዳር ወር 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የግብረሰዶም ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቶ ነበር። በርካታ ግለሰቦች በዚህ ድርጊት የሚታወቁ ሰዎችና ቦታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገፆች እያጋለጡ፤ አልፎም አልፎም ይዘው ሲደበድቡ የሚያሳዩ ምስሎች መቅረባቸውን ተከትሎ ፖሊስ ጥቆማ አድርሱኝ ሲል መግለጫ አውጥቶ ነበር። የተለያዩ መዝናኛ ቦታዎችም በማህበረሰቡ ጥቆማ በፖሊስ ሲያዙ እና ቅጣት ሲደርስባቸው እነሱን ሲያስተናግዱ የነበሩ ቦታዎችም ሲታሸጉም ቆይቷል።


ይህ አይነት ነገር በምንም መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ አይሆንም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም “የሞት አዋጅ” ያፀድቃል ብሎ ማሰብ ይከበዳል፤ ከሆነ ግን የከፈለው ዋጋ ይከፈላል እንጂ ተግባራዊ እንዳይደረግ ቁርጠኝነታችን ይቀጥላል ሲሉ የማህበሩ ሰብሳቢ አሳስበዋል፡፡


የኢትዩጵያን ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ “ጋብቻ አሁንም ወደፊትም በሴት እና በወንድመካከል ብቻየሚፈፀም ቅዱስሚስጢር ነው”ሲል ማስታወቁ ይታወሳል። የኢትዩጵያን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተመሳሳይ ጾታ ለሚደረግ ማንኛውም ነገር ፈቃድም ሆነ ቡራኬ እንደማትሰጥም አስታውቃለች።


የአፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ሕብረት (ሴካም) በጉዳዩ ላይ ከሰሞኑ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የሮማ ሊቀ ጳጳስ ኣባ ፍራንሲስ ተመሳሳይ ፆታ ጥንዶችን በተመለከተ ያወጡትን አዋጅ ውድቅ አድርገው በተመሳሳይ ጾታ የሚፈጸም ህብረት “ከአምለክ ፈቃድ ጋር የሚቃረን” ነው ብሏል ፡፡


የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ መፍቀዳቸው ይታወሳል ፡፡


የሮማ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ ሰጡ


የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ከሳምንት በፊት የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ መስጠታቸው ተገልፅዋል። ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ አዲሱን የቫቲካን መመሪያ የሚያትቱ መዛግብትን ማፀድቃቸውን ተከትሎ ነበር የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ መስጠታቸው የተሰማው። ፖፕ ፍራንሲስ፤ የቤተ-ክርስትያኒቱ ቄሶች የተመሳሳይ ፆታ “ያልተለመዱ” ጥንዶችን በአንዳንድ ሁኔታዎች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቅጃለሁ ሲሉ ተሰምተዋል።

ቫቲካን ይህንን ተከትሎ በሰጠው ማብራሪያ ይህ የሚሆነው በተለምዶ በቤተክርስትያኗ በሚካሄዱ ሥነ-ሥርዓቶች ላይ እንዳልሆነ እና አሁንም ቢሆን ትዳር በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚደረግ ሥነ-ሥርዓት እንደሆነ ነው የምናየው ብሏል።


ይህንን ተከትሎም አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ሕብረት (ሴካም)በጉዳዩ ላይ ከሰሞኑ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ የሊቃ ጳጳሱን አዋጅመም ውድቅ ማድረጉነብ አስታውቋል። የአፍሪካ እና የማዳጋስካር ኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤዎች ሕብረት ሴካም)በመወከል በኮንጎ ካርዲናል ፍሪዶሊን አምቦንጎ ተፈርሞ የወጣው መግለጫው፤ በተመሳሳይ ጾታ የሚፈጸም ህብረት “ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚቃረን” ነው ብሏል። ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በተመለከተ ከቫቲካን የወጣው አዋጅ የአፍሪካውያን ብል እና እሴትን የሚጥስ እንደሆነም የአፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ህብረት አስታውቋል። ሴካም ከጋና ዋና ከተማ አክራ በሰጠው መግለጫ “በክርስቲያናዊ ጋብቻ እና ግንኙነት ላይ ያለው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አልተለወጠም”ብሏል። "በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ጳጳሳት በአፍሪካ የተመሳሳይ ጾታ ጥንዶችን መባረክ ተገቢ ነው ብለን አንወስደውም" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።


የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረመው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማሳሰቧ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፤ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን እንደማትባርክ መግለጿ ይታወሳል። “ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም፤ አታጸድቅም”ያለው መግለጫው ጋብቻ ማለት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚደረግ ህብረት መሆኑን አስረድቷል።


የሮማ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የቤተክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ ሰጡ የሚለው መረጃ መሰማቱን ተከትሎ የተለያዩ ድጋፎችና ተቃውሞዎችን አስተናግዷል። የዩክሬን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቫቲካን የቤተክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠትን አስመልክቶ ያወጣውን ውሳኔ እንደማትቀበል አስተውቃለች። በተቃራኒው ከቫቲካን የተሰማው ዜና በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።





7 views0 comments

Comments


Post: Blog2 Post
bottom of page