ጾታዊ ጥቃትን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በመቅረጽ የሚቸበቸብባቸው ስውር የበይነ መረብ ግብይቶች
- Adiheni multimedia provisions
- Sep 23, 2023
- 2 min read
Updated: Oct 4, 2023
ከዕለቱ ዜናዎችና መረጃዎች የተቀነጨበ 👉 ያድምጡ AH online radio & Podcast
ጾታዊ ጥቃትን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በመቅረጽ የሚቸበቸብባቸው ስውር የበይነ መረብ ግብይቶች
👉የስልካችን ቪድዮዎችና ፎቶዎች በስውር የሚሰረቁበት ሁኔታና አደጋዎቹ
👉በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የተነሱ፣ ጾታዊ ጥቃትን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በሀከሮች እጅ መግባት እንዴት? ለምን?
ጾታዊ ጥቃትን የሚያሳዩና ወስባዊ ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎች ሠዎች ሳያውቁት ዕየተቀዳ ለዚሁ አላማ በተዘጋጁና በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ ድረገፆች ላይ ይሸጣሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ቢቢሲ በምስራቅ ኢስያ ያለውን በማጥናት የደረሰበትን እንደሚከተለው ይገልፃል፡፡
በምሥራቅ እስያ ሴቶች ላይ የጾታዊ ጥቃት ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎችበድብቅ እየቀረጹ በስውርየበይነ መረብ መድረኮችላይ ለተመልካቾች በገንዘብይሸጣሉ። ቪዲዮዎቹ የሚቀረጹት ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው በባቡሮች፣ በአውቶብሶች እና በሌሎችም አካባቢዎች ነው። ቪዲዮዎቹ በዋናነት “አንክል ኩዊ” በሚባልሰው እና ግብረ አበሮቹ ተቀርጸው በድረ ገጽ የሚሸጡ መሆናቸውቢቢሲ አረጋግጧል። የቢቢሲን ቪዲዮ ከላይ ማየት ይቻላል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ቪድዮዎች ሆን ተብሎ የሚቀዳና አንደኛው ወገን ሳያውቅ የሚፈጸሙ አሊያም ሁለቱም ወገኖች ሳያውቁት ቅጂው የሚተላለፍና የሚሸጥ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሠዎች፣ በተለያየ አጋጣሚ በስልካችሁ ቪዲዮዎችንና ፎቶዎችን በማንሳት የሚያስቀምጡ ሲሆን እነዚህን ፎቶዎች በሀከሮች በሚወሰዱበት ጊዜ ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን በመለየት በነዚህ ስውር ድረ ገጾች ላይ እንዲለጠፉ ይሆናል፡፡ ሀከሮቹ እነዚህን መረጃዎች ከስልካችን ላይ የሚወስዱት እንዴት ነው?

እንደሚታወቀው ስልካችን ላይ የተለያዩ APPs መተግበሪያዎች እንጭናለን፡፡ ጌሞችን ጨምሮ ስንጭን ብዙዎች የማያጣሩትና የሚዘነጉት ነገር ምንድነው? የመተግበሪያውን ፍቃድ/permission ማስተካከያ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የመኪና ጌም፤ ለልጃችን ይሆናል፣ ስንጭን፣ ያኔ permission የሚለውን ለሁሉም ማለትም ለፎቶ፣ ለኮንታክት…. የስ የስ በማለት የምንጭን ሲሆን በርግጥ፣ ለመኪና ጌም ፎቶና ኮንታክት ምን እንደሚያደርግ ሳናስተውል እንቀራለን፡፡ ጌሙ ቢሰራም በስልካችን ላይ የሚገኙትን ፎቶዎች የማግኘት ፍቃድ ያገኘው መተግበሪያ ኢንተርኔት ሲያገኝ ሁለተኛውን ስራ ለአዘጋጆቹ ማስተላለፍ ይጀምራል፡፡ በዚህ መንገድ ስልካችን ላይ ያሉት መረጃዎች እኛ ሳናውቅ ወደ ሌሎች ይተላለፋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የማይታወቁ ሊንኮች ሲላኩልን መጫንና ሳያስተውሉ መነካካት ለተመሳሳይ ችግር ሊያጋልጥ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡

በሀገራችን ለዚህ ማስረጃ የሚሆን ክስተቶች አሉ፡፡ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በተለያዩ አጋጣሚ በተለያዩ ሠዎች የተቀረጹ ፆታዊ ጥቃትን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በነዚህ ስውር ድረ ገጾች ላይ መውጣታቸው እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ይህም ሠላም ከተፈጠረ በኋላ እንዚህ ፎቶዋችና ቪዲዮዎች ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በተለያየ አጋጣሚ ሳይጠፉ ተቀምጠው ሳለ ኢንተርኔት መጠቀም ሲጀምሩ ለሀከሮቹ እንደተጋለጡ ይታመናል፡፡
コメント